የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ባለድርሻ አካላት የልምምድ ልውውጥ አለማድረግና የግንዛቤ ዕጥረት በዘርፉ በስፋት የሚስተዋሉ ችግሮች መሆናቸውን ኤፍ ኤስ ዲ ኢትዮጵያ አስታውቋል።
ኤፍ ኤስ ዲ ኢትዮጵያ ችግሩን ለመቀነስ በፋይናንስ ዘርፍ ከተሰማሩ ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ በሸራተን አዲስ እየመከረ ይገኛል።
የኤፍ ኤስ ዲ ኢትዮጵያ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤርሚያስ እሸቱ ፣በዘርፉ ፈጠራን በማበረታታት ምቹ ሁኔታን መፍጠር ያስፈልጋል ብለዋል።
በተለይም በኢንሹራንስ ዘርፍ የሚስተዋለውን የግንዛቤ ዕጥረትና የልምድ ልውውጥ ችግር ለመፍታት ባለድርሻ አካላት በትኩረት መስራት እንዳለባቸው አንስተዋል።

የብሔራዊ ባንክ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ ሰለሞን ደስታ በበኩላቸው፣ የኢንሹራንስ ኢንዱስትሪዎች የሚገጥማቸውን ችግሮች ለመፍታት የቴክኖሎጂ ፈጠራዎችንና አዳዲስ አሰራሮችን መከተል እንደሚገባ አሳስበዋል።
“ኢኖቬሽን ፎር ሪዚሊየንስ” በሚል ርዕስ እየተካሄደ ያለው መድረክ ኤፍ ኤስ ዲ ኢትዮጵያ ከኤፍ ኤስ ዲ አፍሪካና ከብሔራዊ ባንክ ጋር በጋራ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።
ኤፍ ኤስ ዲ ኢትዮጵያ ሁሉን ያካተተ የፋይናንሺያል ገበያን ለማስፋት እየሰራ እንደሚገኝም በዚሁ መድረክ ላይ አስታውቋል።
በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 07 ቀን 2015 ዓ.ም











