ዩክሬን ተተኳሽ ጥይቶችንና የጦር መሳሪያ ቅሪቶችን ከግዛቷ ለማስወገድ ከ7መቶ ዓመት በላይ ይፈጅባታል ተባለ::

ሀገረ ዩክሬን በጦርነቱ ምክንያት አብዛኛዉ ግዛቷ በጦር መሳሪያ ቅሪቶችና በተተኳሽ ጥይቶች በመሸፈኑ ይህንን ለቅሞ ለማስወገድ 7 መቶ 57 ዓመት እንደሚወስድባት አንድ ጥናት አመልክቷል፡፡

ጦርነቱ ዩክሬንን በአለማችን በማዕድን የተሸፈነች ሀገር እንዳደረጋትም ሪፖርቱ አስታዉቋል፡፡
አንድ ሶስተኛ የሚሆነዉ የዩክሬን ግዛት የጦርነቱ ሰለባ መሆኑን የገለጸዉ ጥናቱ ፤ ይህም ብዙ በተቀጣጣይና መርዛማ የጦር መሳሪያ ቅሪቶች የተሸፈነ ነዉ ተብሏል፡፡

በቁጥር ሲገለፅም 1 መቶ 73 ሺህ 5መቶ 29 ስኩዌር ኪሎ ሜትር ይሸፍናል፤ ይህም ከዩራጓይ የቆዳ ስፋት እኩል እንደማለት ነዉ፡፡
እነዚህ ተቀጣጣይና ያልፈነዱ የጦር መሳሪያ ቅሪቶች ከ 3 መቶ በላይ ንጹሃንን እንደገደሉ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሪፖርት ያመላክታል፡፡

ዩክሬን በእነዚህ አደገኛ የጦር መሳሪያ ቅሪቶች እንደትወረር የእነ አሜሪካ የጦር መሳሪያ ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋዕፅኦ እንዳደረጉም አርቲ ኒዉስ ዘግቧል፡፡
የክላስተር ቦምቦች ፍንጥርጣሪ ደግሞ ለቀጣዩ የዩክሬን ትለዉልድ አደጋ እደሚሆንም ድርጅቱ አስጠንቅቋል፡፡

አሜሪካ እነዚህ የጦር መሳሪያ ፍንጥርጣሪና ተቀጣጣዮችን ለመልቀም የሚደረገዉን ጥረት ለመደገፍ 95 ሚሊን ዶላር ድጋፍ ማድረጓም ተሰምቷል፡፡
እናም ዩክሬናዉያን በጦርነቱ ወቅት ብቻም ሳይሆን ከጦርነቱ በኋላም የከፋ ችግር እያንዣበባቸዉ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ
ሐምሌ 17 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *