ቡና ባንክ ለሶስተኛ ጊዜ ያዘጋጀው የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች የይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር አሸናፊዎችን ይፋ አደረገ።

ባንኩ ሶስተኛውን ዙር የመምህራንና የጤና ባለሙያዎች ይቆጥቡ ይሸለሙ መርሃ ግብር መጠናቀቅ ምክንያት በማድረግ በመርሃ ግብሩ ላይ ተሳታፊ የሆኑ የሽልማት አሸናፊ ደንበኞቹን በዕጣ ለይቷል።

በዚህም መሰረት የቤት መኪና የሚያሸልመው አንደኛ የእጣ ቁጥር 8074368 ሆኖ ወጥቷል።

ላፕቶፕ ኮምፒውተር የሚያሽልመው ሁለተኛ የአሸናፊ እጣ ቁጥር ደግሞ 9614144 ሆኖ የወጣ ሲሆን ታብሌት የሚያሸልመው ሶስተኛ የአሸናፊ እጣ ቁጥር 3467580 ሆኖ ሊወጣ ችሏል።

የቡና ባንክ የኮርፖሬት ኮሚኒኬሽን ዳሬክተር አቶ መላኩ ብርሀኑ እንደተናገሩት የዜጎችን ቁጠባን በማበረታታት የሃገርን ኢኮኖሚ መገንባት የፋይናንስ ተቋማት ሃላፊነት ነው ብለዋል።

ቡና ባንክ በተለይም ለማህበረሰቡ ፋይዳ ያላቸው ሙያዎች ባለቤት የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ለቁጠባ የሚያነሳሳ ማበረታቻ በመቅረጽ ተጠቃሚ ማድረግ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 21 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.