የሩስያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለፕሬዝዳንት ምናንጋግዋ ዘመናዊ ሂሊኮፕተር አበርክተዋል፡፡
በሩስያ እየተካሄደ በሚገኝው የሩስያ አፍሪካ ስብሰባ ላይ የተገኙት የዚምባብዌው ፕሬዝዳንት ከፑቲን ተገናኝተው መክረዋል፡፡
ከአውሮፓ ህብረት እና ከአሜሪካ በርካታ ማዕቀቦች የተጣሉባቸው የዚምባብዌ ባለስልጣናት ከሩስያ ጋር ያላቸውን ወዳጅነት እያጎለበቱ ይገኛሉ፡፡
ሩስያ የሚገኙት ኤመርሰን ምናንጋግዋ ሩስያ ዚምባብዌ ወዳጅ ሀገር መሆኗ ማንም የሚያውቀው ነው ከንግዲህ ማንም ሊያበላሸው አይችልም ብለዋል፡፡
ከፑቲን የተበረከትላቸው ዘመናዊ ሂሊኮፕተር አስመልክተው እንደተናገሩትም ከወደጃችን የተበረከተልን ዘመናዊ ሂሊኮፕተር ለኛ ብዙ ትረርጉም አለው ብለዋል፡፡
በአውሮፓ እንደዚሁም በአሜሪካ የማዕቀብ ሰለባ የሆኑ ሃገራት መተባበር አለባቸው” ሲሉ ምናንጋግዋ ከሄሊኮፕተሩ ፊት ለፊት ቆመው ንግግር አድርገዋል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሐምሌ 21 ቀን 2015 ዓ.ም











