የመንግስት ግዥ እና ንበረት ባለስልጣን የግዥ ስርዓትን ለማዘመን ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር እየሰራ መሆኑን ገለጸ፡፡

ባለስልጣኑ በቀጣዩ ነሃሴ ወር በጎንደር ከተማ በሃገሪቱ ከሚገኙ የመንግሰት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ውይይት እንደሚያደርግም ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግሯል፡፡
169 የፌደራል ተቋማትን በኤሌክትሮኒክስ የግዢ ስርዓት ውስጥ እንዲካተቱ ማድረጉን የገለጸው ባለስልጣኑ፣ቀጣይ እርምጃው የመንግስት ዩንቨርሲቲዎችን በዚህ ስርዓት እንዲካተቱ ማድረግ መሆኑንም ገልጿል፡፡

ለዚህም ከነሃሴ 19 እስከ 21 ድረስ በጎንደር ከተማ ከሁሉም የመንግሰት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር ወይይት እንደሚያደርግ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ ሃጂ ኢብሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

የከፍተኛ ትምህርት ተቋማቱ በኤሌክትሮኒክስ የግብይት ስርዓት ውስጥ ለመካተት በቂ አቅም አላቸው ያሉት ሃላፊው ፤እንደጉድለት ሊነሳ የሚችለው የግንዛቤ ችግር ነው ብለዋል፡፡
ለዚህም ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በጎንደር ከተማ ለሶስት ቀናት የሚካሄደውን ውይይት ጨምሮ በተለያዩ አጋጣሚዎች ለተቋማቱ ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝም አንስተዋል፡፡

በአዲስ አበባ የሚገኙ፤የአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ ፤ የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ፤ሜትሮፖሊቲያን እና ሲቪል ሰርቪስ ዩንቨርስቲዎች ወደ ኤሌክትሮኒክስ ግዢ ስርዓቱ መካተታቸውን አቶ ሃጂ ኢብሳ ጠቅሰዋል፡፡

የአብዛኛዎቹ የከፈተኛ ትምህርት ተቋማት መገኛቸው ከመዲናዋ ውጭ በመሆኑ ሰፊ ስራዎችን መስራት እንደሚጠበቅም ዳይሬክተሩ ገልጸዋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን

ሐምሌ 26 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.