አቢሲንያ ባንክ 4ኛ ዙር መቆጠብ ያሸልማልና የ5ኛ ዙር እንሸልምዎ መርሃ ግብር ዕድለኞችን በዛሬው እለት ይፋ አድርጓል፡፡

ባንኩ በሁለቱ ዘርፎች አሸናፊ የሆኑትን ባለ ዕድለኞች በብሔራዊ ሎተሪ አስተዳዳር በተደረገ የዕጣ ማውጣት ስነ ስርአት ነው ይፋ ያደረገው፡፡

አቢሲንያ ባንክ የቁጠባ ባህልን ለማዳበርና የውጭ ምንዛሬን ለማስገኘት በሚል የ4ኛ ዙር “መቆጠብ ያሸልማል” እንዲሁም የ5ኛ ዙር “እንሸልምዎ” መርሃ ግብሩን ነው በዛሬው ዕለት ይፋ ያደረገው።

እነዚህ መርሃ ግብሮች ለ6 ወር መቆየታቸውን የባንኩ ኃላፊዎች በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

በመቆጠብ ያሻልማልና በእንሸልምዎ መርሃ ግብር አጠቃላይ 8 ሚሊዮን 49 ሺህ ዕጣዎች እንደተዘጋጁም ታውቋል።

የአቢሲንያ ባንክ ምክትል የሪቴሌር ኃላፊ አቶ ወሰንየለህ አበራ ፣ባንኩ የህብረተሰቡን የቁጠባ ባህል ለማሳደግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል።

በተጨማሪም በህጋዊ መንገድ የውጭ ምንዛሬ ወደ ሀገሪቱ እንዲገባ የማበረታቻ መርሃ ግብርሮችን ለደንበኞቹ እያሰፋ ይሄዳል ነው ያሉት።

ባንኩ በ2030 በምስራቅ አፍሪካ ተወዳዳሪ ባንክ ለመሆን እየሰራ እንደሚገኝና ከ8 መቶ በላይ ቅርንጫፎች እንዳሉትም አንስተዋል።
ባንኩ ይፋ ባደረገው ሽልማት አይሱዙ መኪና፣ትራክተር

ለሁለት ደንበኞች በቱርክ ሀገር የአምስት ቀን የሽርሽር ቆይታ፣ አይፎን ስልኮች ፣ ላፕቶፕ ጄነሬተር፣ እና ሌሎችም ሽልማቶች ይገኙበታል።

በአባቱ መረቀ

ነሃሴ 04 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.