የመሬት አገልግሎት ዕግድ ተነሳ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመሬት ልማትና አስተዳደር ቢሮ ፤ ከቢሮ ሪፎርም ስራ ጋር በተገናኘ በቀን 28/11/2015 ለሁሉም ክፍለ ከተሞች የመሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት በተላከ ደብዳቤ የመሬት አገልግሎት መታገዱ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ የዕገዳው መነሳት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ከዛሬ ነሐሴ 8/2015 ዓ.ም ጀምሮ ዕግዱ የተነሳ መሆኑን በዶ/ር ቀነዓ ያደታ (የመሬት ልማት አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ) ተፈርሞ ለሁሉም ክ/ከተሞች የመሬት ልማትና አስተዳደር ፅ/ቤት የተላከ ደብዳቤ ያሳያል።
ኃላፊው፤አገልግሎቶቹ ሕጋዊ አሰራሮችን በመከተል እንዲሰጡ አሳስበዋል።

(ደብዳቤው ከአዲስ አበባ ከተማ የመሬት መረጃ አገልግሎት የተገኘ ነው)

ነሃሴ 08 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.