ርችት መተኮስ ክልክል ነው


የቡሄ በዓልን ምክንያት በማድረግ በየአካባቢው በሚከናወነው የችቦ ማብራት ስነ ስርዓት ወቅት ርችት መተኮስ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል፡፡

የከተማችንን ሰላም በዘላቂነት ለማረጋገጥ የአዲስ አበባ ፖሊስ ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ውጤታማ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ይታወቃል፡፡

ይህንኑ የፀጥታ ስራ በአግባቡ ለመምራት እና ለመቆጣጠር ሲባል እንዲሁም አጋጣሚውን በመጠቀም ሊፈፀሙ የሚችሉ ህገ-ወጥ ድርጊቶችን ለመከላከል በቡሄ በዓል የችቦ ማብራት ስነ ስርዓት ወቅት ርችት መተኮስ ክልክል መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን ያስተላልፋል፡፡

(የአዲስ አበባ ፖሊስ)

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.