ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ አል ናህንያን አዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ በኢትዮጵያ ቆይታቸውም ከተለያዩ የመንግስት የስራ ኃፊዎች ጋር ተገናኝተው እንደሚወያዩ ይጠበቃል።
ሼክ መሃመድ ቢን ዛይድ የአረብ ኢምሬትስ ፕሬዝዳንት ከሆኑ በኋላ በኢትዮጵያ ጉብኝት ሲያደርጉ ይህ የመጀመሪያቸው ነው፤ ከዚህ ቀደም የቡዳቢ አልጋ ወራሽ በነበሩትበት ወቅት በ2018 በኢትዮጵያ ጉብኝት አድርገው ነበር።
ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ነሃሴ 12 ቀን 2015 ዓ.ም











