ጋና ከስፖርት አወራራጅ ድርጅቶች ከፍተኛ ገንዘብ የሚያሸነፉ ዜጎች 10 በመቶ ታክስ እንዲከፍሉ ወሰነች፡፡

ምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ጋና ዜጎች ከስፖርት አወራራጆች ገንዘብ ሲያሸንፉ 10 በመቶ ታክስ እንዲከፍሉ ውሳኔ አሳልፋለች፡፡

የጋና የገቢዎች ባለስልጣን እንዳሳወቀው ከሆነ፣ በሃገሪቱ የሚገኙ ሁሉም የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶች ለዚህ አሰራር እንዲያመች አሰራራቸውን ማሻሻል እና በየጊዜው የሚጠቀሙትን ሶፍትዌር ማዘመን አለባቸው ብሏል፡፡

በጋና በርካታ ቁጥር ያላቸው የስፖርት አወራራጅ ድርጅቶች ያሉ ሲሆን፣ እነዚህን ድርጅቶች ለመቆጣጠር ሃገሪቷ ጥብቅ ህግ እንዳወጣችም ይነገራል፡፡

ይህ ህግ በጋና ወጣቶች ዘንድ ትችት የቀረበበት ሲሆን፣ ብዙውን ጊዜ በአወራራጅ ድርጅቶች የሚጫወቱ ዜጎች ስራ አጥ ዜጎች መሆናቸው ይነገራል፡፡

የሃገሪቱ ባለስለጣናት በበኩላቸው ይህ ህግ የወጣው አወራራጅ ድርጅቶችን ለመቆጣጠር ታስቦ ነው ብለዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ነሃሴ 12 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.