እስካሁንም በተመሳሳይ በጷጉሜ ወቅት በሰራው የበጎ አድራጎት ዘመቻም ከ52 ሺህ በላይ ሰዎችን ተጠቃሚ ማድረጉን የውዳሴ ዲያግኖስቲክ ማዕከል መስራች እና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ዳዊት ሃይሉ ተናግረዋል።
ዶ/ር ዳዊት እንዳሉት በ”ጷግሜ የጤና” የነፃ የሕክምና ምርመራ ተጠቃሚ የሚሆኑት ከመንግስት የሕክምና ተቋማት የሲቲ ስካን ፣የኤም አር አይ ፣ የአልትራ ሳውንድ እና የላብራቶሪ ምርመራዎችን እና ሌሎች በማዕከሉ የሚሰጡ ምርመራዎችን ለማድረግ በሐኪም የተፃፈ ማዘዣ ያላቸው እና በአቅም ማነስ ምክንያት መመርመር ያልቻሉ ሊሆኑ ይገባልም ብለዋል።

ማዕከሉ የተመሰረተው በ2002 ሲሆን “ጷግሜ የጤና” የበጎ አድራጎት ስራውን ማከናወን ከጀመረም 14 ተኛ አመቱን መያዙንም አንስተዋል።
የነፃ ህክምናውን ለማግኘትም ከነሃሴ 16 እስከ 30/2015 በሚገኙት ቀናት ውስጥ በድርጅቱ ስልክ በ 988, 0940 040404 ወይም 0940 050505 በመደወል መመዝገብ እንደሚችሉ ዛሬ በማዕከሉ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።
ረድኤት ገበየሁ
ነሃሴ 15 ቀን 2015 ዓ.ም











