በሀገሪቱ ያለው ወቅታዊ ሁኔታ አሳሳቢ ሁኔታ ላይ ደርሷል ሲሉ የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አዲሱ ሰብሳቢ አቶ ደስታ ዲንቃ ተናገሩ፡፡

በሀገሪቱ ያሉ ፖለቲካዊ፣ኢኮኖሚ እና ማህበራዊ ጉዳዮች ያሳስበናል ያሉት አዲሱ ሰብሳቢ አቶ ደስታ፣ የጋራ ም/ቤቱ በግጭት ውስጥ ያሉ አካላትን የማቀራረብ ስራ እንደሚሰራ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ ተናግረዋል፡፡

ወደ ዲሞክራሲ እና ወደ አዲስ የፖለቲካ ባህል የሚወስደንን መንገዶች እንጠቀማለን ያሉ አተ ደስታ አዲስ የተቋቋመው ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴም በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ቁርጠኛ ሆኖ ይሰራል ብለዋል፡፡

በተለይም በአማራ ክልል ያለውን አለመረጋጋትና በመላው ሀገሪቱ ያለውን ችግሮች ጨምሮ የጋራ ምክር ቤቱ አፅንኦት ሰጥቶ እንደሚሰራ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡

በአሁን ሰዓት በሀገሪቱ ያልተጓዳ የሚባል አካባቢ የለም ያሉት አቶ ደስታ፣ በቅርቡ ወደ ስራ የሚገባው አዲሱ ስራ አስፈፃሚ ትኩረቱን እዚህ ላይ አድርጎ ይሰራል ብለዋል፡፡
የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ዓመታዊ ጉባዔውን ነሐሴ 13 ቀን 2015 ዓ.ም ማከናወኑ የተገለፀ ሲሆን አዲስ የስራ አስፈፃሚ አባላትንም መርጧል፡፡

በዚህም አቶ ደስታ ዲንቃ ከመድረክ የጋራ የምክር ቤቱ ሰብሳቢ፣አቶ መለስ አለሙ ከብልፅግና ምክትል ሰብሳቢ እና ወይዘሮ ደስታ ጥላሁን ከኢህአፓ ፀሀፊ በመሆን ተመርጠዋል፡፡
የቀድሞ የምክር ቤቱ ስብሳቢ የነበሩት ዶክተር መብራቱ ዓለሙ ከቦዴፓ እና ሙሳ አደም ከአህፓ አባል በመሆን ተመርጠዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ነሃሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.