“በኢትዮጵያ 52 በመቶ የሞት ምጣኔ የሚከሰተው ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች ነው”—–የጤና ልማትና ፀረ ወባ ማህበር፤

ማህበሩ የተመሰረተበትን 25ኛ ዓመቱን በዛሬው እለት እያከበረ ይገኛል፡፡

የተመሰረተበትን 25ኛ አመት እያከበረ ባለበት በዚሁ መድረክም፣ ኢትዮጵያ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች አምራች ዜጎቿን እያጣችና የኢኮኖሚ እድገቷ እየተገታ ከመሆኑም ባሻገር ለነዚህ ህመሞችም በየዓመቱ በቢሊዮን የሚቆጠር ብር እንደምታወጣ አስታዉቋል።

በዚህም ኢትዮጵያ ተላላፊ ባልሆኑ በሽታዎች መስፋፋት ምክንያት ብቻ ከ 31 ቢሊዮን ብር በላይ ማጣቷን ነው ማህበሩ ያስታወቀው፡፡

ይህም ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 1.84 በመቶ አካባቢ እንደሚይዝ የማህበሩ መግለጫ ያስረዳል፡፡

ማህበሩ በ1990 የተመሰረተ ሲሆን 25 ዓመታትን ወባን ለማጥፋት፣ የኤች አይቪ/ኤድስን ስርጭትን ለመቆጣጠር፣ዋና ዋና ተላላፊ ያልሆኑ እና ተላላፊ የሆኑ በሽታዎችን ለመከላከል በትኩረት ሲሰራ እንደነበር የማህበሩ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ዶ/ር አበረ ምህረቴ አንስተዋል።

ማህበሩ በአሁኑ ወቅት ከ260 ሺህ በላይ አባላት እና በጎ ፈቃደኞች እንዳሉት መረጃዎች ያመለክታሉ።

ረድኤት ገበየሁ

ነሃሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.