ኢትዮጵያ በግብር አማካኝነት የምታገኘው ገቢ ከጎረቤት ሃገራት ጋር ሲነጻጸር እጅጉን አነስተኛ መሆኑን በገንዘብ ሚኒስቴር የታክስ አማካሪ አቶ ዋሲውን አባተ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡
ጎረቤት ሀገር ኬንያ ከአጠቃላይ ሃገራዊ ገቢዋ፤የግብር ገቢ ከ18 በመቶ የበለጠውን እንደሚሸፍንላት አንስተዋል፡፡
ኢትዮጵያ ግን ከአጠቃላይ አመታዊ ገቢዋ መካከል፤ከግብር የምታገኘው ከ10 በመቶ በታች ነው ሲሉ አቶ ዋሲውን ተናግረዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ አንደ ዋና ምክንያት ያነሱት የሃገራችን የታክስ ህጎች በየጊዜው የማይታዩና ከወቅቱ ጋር እንዲሄዱ ሆነው አለመሻሻላቸው መሆኑ ነው፡፡
ይህም ግብርን የመሰወር ተግባራትን እንዳበዛ እና ሃገር ከግብር ልታገኝ የሚገባትን ገቢ እንዳሳጣት ገልጸዋል፡፡
ለዚህ ደግሞ ዋናው መፍትሔ፤በየጊዜው የታክስ ህጉን መመልከት እና ክፍተቱን ለመሙላት ጥረት ማድረግ እንደሆነ የታክስ ባለሞያው አቶ ዋሲውን አባተ ተናግረዋል፡፡
በመሳይ ገ/መድህን
ነሃሴ 17 ቀን 2015 ዓ.ም











