አንዳንድ የስራ ሃላፊዎች አምቡላንስን ከታለመላቸው ዓላማ ውጭ ይጠቀማሉ….ጤና ሚንስቴር

ይህን ሲያደርጉ ቢገኙ እርምጃ እወስዳለሁ ሚንስቴሩ

በሀገሪቱ ያሉ አምቡላንሶችን ለሌላ አላማ የሚጠቀሙ የስራ ሃላፊዎች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ።

በሰሜኑ ጦርነት ምክንያት በርካታ የሆኑ አምቡላንሶች እንደተጎዱበትም ሚንስቴሩ አስታዉቋል።

በጤና ሚኒስቴር የሜዲካል አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶክተር ኢሊባቡር ቡኖ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ በሀገሪቱ ያሉት አምቡላንሶች ከ4 ሺህ የማይበልጡ ሲሆን ከዚህ ዉስጥም 800 የሚሆኑት አገልግሎት እየሰጡ እንዳልሆነ ተናግረዋል።

ሆስፒታልን ከሆስፒታል በማገናኘት በተለይም በአፋር፣አማራ፣ትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች የተጎዱ አካባቢዎች ያሉ አምቡላንሶቸ ግብዓት እንዲሟላ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል።

ተደራሽነቱ ላይ በተለይም እርሳቸዉ የሚመሩት ተቋም ትኩረት አድርጎ እየሰራ መሆኑን ነው የተናገሩት።

ሌላዉ አሳሳቢ ነገር አምቡላንሶችን ከታለመላቸዉ አላማ ዉጪ የሚጠቀሙ የስራ ሃላፊዎች መኖራቸዉ ነው ያሉት ሃላፊው ይህም ከፍተኛ ተግዳሮት እንደሆነባቸዉ አንስተዋል።

ይህን እኩይ ድርጊት ሲፈጽሙ የተገኙ ሀላፊዎች ላይም እርምጃ እንደሚወሰድባቸዉ ዶክተር ኤሊባቡር ተናግረዋል።

በአቤል ደጀኔ

ነሃሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.