ከተማዋን የሚመጥኑ የመልዕክት ማስተላለፊያ መንገዶች ያስፈልጋሉ የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን!

ኢሳያስ ማስታወቂያ፣ከሁለት ሚሊዮን ብር በላይ ወጭ በማድረግ አራት ኪሎ አደባባይ አካባቢ ዝግጁ ያደረገውን የዲጂታል ማስታወቂያ ስክሪን ዛሬ ወደ ስራ እንዲገባ አድርጓል፡፡

በማስጀመሪያ ስነ ስርዓቱ ላይ ከከተማ አስተዳደሩ የተወከሉ ሃላፊዎችና ሌሎችም እንግዶች ተገኝተው ነበር፡፡

ድርጅቱ በከተማ አስተዳደሩ ባገኘው የማስታወቂያ ቦታ ከሁለት መቶ ሚሊዬን ብር በላይ ዘመናዊ የዲጅታል ማስታወቂያ ስክሪን አራት ኪሎ አደባባይ ላይ አስገጥሞ ለአገልግሎት ብቁ ምድረጉን አስታውቋል።

ኢሳያስ ማስታወቂያ ስራዎች በሃገሪቱ ካሉ ጠንካራ የማስታወቂያ ስራ ድርጅቶች መካከል አንዱ ሲሆን በርካታ የማስታወቂያ ስራዎችን በመስራት የሚታወቅ መሆኑ መስነ ስርዓቱ ላይ ተነስቷል።

ኢሳያስ ማስታወቂያ የዲጅታል ማስታወቂያ ስክሪን ባሁኑ ሰአት አራት ኪሎ ላይ ያስገጠመ ሲሆን በከተማው በ25 ቦታዎችም ለመግጠም መዘጋጀቱን ተናግሯል።

በምረቃ ስነ ስርአቱ ላይ የተገኙት የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ዳሬክተር አቶ ዳዊት ሁንዴሳ፣ ዘመናዊ የሆኑ የመልእክት ማስተላለፍያዎች የከተማዋን ውበት ከመጠበቅ አንጻር ሚናቸው የጎላ ነው ብለዋል።

በሌላ መልኩ ደግሞ መልእክቶች ባልተገባ መንገድ እንዳይተላለፍ ቁጥጥሩን ማጥበቅ ያስፈልጋል ብለዋል።

ዘመናዊ ከተማ ለመገንባት ዘመናዊ የመልእክት ማስተላለፍያዎች ሊኖሩ ይገባል ያሉት ዳሬክተሩ፣ ሌሎችም ተመሳሳይ ድርጅቶች ይህንን መንገድ እንዲከተሉ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሃሴ 18 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.