ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ አ.ማ ከተለያዩ ባንኮች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ተፈራርመ።

የዲጂታል ብድር አገልግሎትን የተመለከተ አወደ ጥናትም አስጀምሯል።

ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ አ.ማ በዲጂታል አማራጭ የሚቀርቡ አነስተኛ ብድሮች ላይ ያተኮረ አውደ ጥናት እና ምንም አይነት መያዣ የማይጠየቅባቸው የዲጂታል ብድር አገልግሎቶችን ለማስጀመር ከተለያዩ ባንኮች ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን የስምምነት በዛሬዉ ዕለት ተፈራርሟል።

ካቻ የመጀመሪያው የግል የክፍያ ሰነድ አውጪ ሆኖ የተሟላ ሥራውን እንዲጀምር በብሄራዊ ባንክ ፈቃድ ካገኘ በኋላ የተደረገው የመጀመርያው ታሪካዊ የሆነ አዉደ ጥናት የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የመንግስት እና የግል ባንኮች እና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች እንዲሁም የኢንዱስትሪው ባለሙያዎች በተገኙበት

ከአውደ ጥናቱ ጎን ለጎን ምንም አይነት መያዣ የማይጠየቅባቸው የዲጂታል ብድር አገልግሎቶች፣ በፋይናንስ ስርኣቱ ውስጥ ተካታች ያልሆነውን የህብረተሰብ ክፍል ለማካተት የሚረዱ ዲጂታል ቁጠባ አገልግሎቶች እንዲሁም የአለምአቀፍ ሃዋላ አገልግሎትን ለሚቀጥሉት 5 ዓመታት በጋራ ለመስራት የሚያስችል ስምምነት የፊርማ ስነ ስርዓትም ከንብ ኢንተርናሸናል ባንክ እና ከግሎባል ባንክ ኦፍ ኢትዮጵያ ጋር ተደርጓል፡፡

የሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎትን ጨምሮ የተለያዩ የክፍያ ሰነዶችን ለማውጣት ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ በቁጥር NPS/PII/002/2022 ፈቃድ ያገኘ የመጀመሪያው የግል የክፍያ ሰነድ አውጪ መሆኑመ ተገልፃል ፡፡

የሞባይል ገንዘብ ዝውውርን እና ሌሎች የፋይናንስ አገልግሎቶችን በተለያየ ደረጃ እና የአገልግሎት መስጫ አማራጮች ማለትም በUSSD አጭር ቁጥር *677# ፣ በአንድሮይድ እና አይ ኦ ኤስ መተግበሪያዎች በመጠቀም የሙከራ ትግበራውን ከማከናወኑ በተጨማሪ በአሁኑ ወቅት ከተለያዩ ባንኮች እና የሞባይል ገንዘብ ዝውውር አገልግሎት ሰጪዎች ጋር ያለውን ተናባቢነት በተሳካ ሁኔታ በማጠናቀቅ አገልግሎቶቹን በሙሉ አቅም ለመጀመር ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ፈቃድም አግኝቷል።

በፊርማ ስነ ስርዓቱ ወቅት የካቻ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ አብረሃም ጥላሁን እንደተናገሩት  “ዲጂታል ብድር ግለሰቦችን እንዲሁም የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን የብድር አግልግሎት ተጠቃሚ በማድረግ የኢኮኖሚ እድገትን እና የፋይናንስ አካታችነትን ለማስፋት ከፍተኛ አቅም እንዳለው እናምናለን ብለዋል።

በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ በኢትዮጵያ ከቀዳሚዎቹ የግል ባንኮች መካከል ስመጥር የሆነው የንብ ኢንተርናሽናል ባንክን ወክለው ተገኙት የባንኩ  ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ አብርሀም ተስፋዬ እንዳሉት “እንደ ባንክ የረጅም አመታት ልምድን፣ የቁጥጥር ማዕቀፎችን፣ ጥልቅ ግንዛቤ እና ጠንካራ የደንበኛ መሰረት ወደዚህ አጋርነት እናመጣለን ሲሉ በአወደ ጥናቱ ላይ ተናግረዋል።

ከሳቸዉ በተጨማሪ  ግሎባል ባንክ ኦፍ ኢትዮጵያን ወክለው የተገኙት የባንኩ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆኑት አቶ ሳህለሚካኤል መኮንን  “ዛሬ የተካሄደው በጋራ የመስራት ስምምነት ባንካችን በተለየ መንገድ ቀርፆ ወደ ትግበራ ያስገባውን የ5 ዓመት ስትራቴጂክ እቅድ መሰረት ከካቻ ጋር በጋራ በዲጂታል አማራጭ የሚቀርቡ አነስተኛ ብድሮችን ወደ ገበያ በማስገባት የጥቃቅን፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች እድገትን በማጎልበት የባንኩን ዘላቂ እድገት የምናረጋግጥበት ይሆናል።” ብለዋል

ካቻ ዲጂታል ፋይናንሺያል ሰርቪስ አ.ማ ከሁለቱ ባንኮች በተጨማሪ በቅርቡ ከሌሎች ባንኮች እና የማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት  ጋር ተመሳሳይ ስምምነቶችን በመፈፀም እና በፍጥነት ወደ ትግበራ የሚገባ መሆኑም ተገልፃል።  

በአቤል ደጀኔ

ነሐሴ 20 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.