የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል በፀጥታ ችግር ምክንያት የአቅርቦት እጥረት እንዳጋጠመዉ አስታወቀ።

በቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል ባለዉ የፀጥታ ሁኔታ ሆስፒታሉ ከፍተኛ የሆነ የግብዓት አቅርቦት እጥረት አጋጥሞታል ተብሏል።

የአሶሳ አጠቃላይ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር መርቀኒ አወድ ከኢትዮ ኤፍ እም ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ከክልሉ ባሻገር በአቅራቢያዉ ባሉ የኦሮሚያ ወረዳዎች ጭምር ያለዉ የፀጥታ ስጋት ሳቢያ ሆስፒታሉ ማስተናገድ ከሚችለዉ ታካሚ በላይ በማስተናገድ ላይ ይገኛል ብለዋል።

በዚህም በክልሉ ባለዉ የፀጥታ ሁኔታ የአቅርቧት እጥረት በከፍተኛ ሁኔታ እየፈተናቸዉ እንደሆነ ይናገራሉ።

ሆስፒታሉ ከፍተኛ የኦክስጅን እጥረት እንዳጋጠመዉና ይህም ለስራቸዉ ፈታኝ እንደሆነባቸዉ ሜዲካል ዳይሬክተሩ ለጣብያችን ተናግረዋል።

ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር እንደ ቤንሻንጉል ባሉ ክልሎች ላይ የክልሉ ህዝብ ባለበት ሆኖ አገልግሎት እንዲያገኝ በተይም እንደ ኦክስጅን፣የላብራቶሪ ዕቃዎችን አሟልቱ አገልግሎት እንዲያገኙ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል።

በክልሉ ከፀጥታ ጋር በተያያዘ በአምቡላንስ ሪፈር ማድረግ ከቆመ ወዲህ ቀጥታ ወደ አዲስ አበባ ታካሚዎችን እየላክን ነዉ ያሉት ዶክተር መርቀኒ በዚህም ህብረተሰቡ ክፉኛ ተማሯል ብለዋል።

በክልሉ በፀጥታ ስጋት ምክንያት ታካሚዎችን በአሞቡላንስ ሪፈር መላክ ከቆመ አራት አመት እንደሆነዉ ሰምተናል።

በአቤል ደጀኔ

ነሐሴ 22 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.