የአፋር ክልል በድንገተኛ ህክምና ከፍተኛ የሞት ምጣኔ የተመዘገበበት ክልል መሆኑን የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የአፋር ከልል ከፍተኛ ድንገተኛ ታካሚዎችን በማስተናገድም ግምባር ቀደም መሆኑን የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ለኢት ኤፍ ኤም አስታውቋል፡፡

በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የሜዲካል አገልግሎት መሪ ስራ አስፈፃሚ የሆኑት ዶክተር ኢሊባቡር ቡኖ ከኢትዮ ኤፍ ኤም ጋር በነበራቸው ቆይታ፣ በክልሉ ያለው የድንገተኛ ህክምና ሞት ከሌሎች ክልሎች ጋር ሲነፃፀር ከፍተኛ ቁጥር ያለው መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ድንገተኛ የጤና እክሎች ከክልል ክልል ከፍያለ መሆኑን የሚገልፁት ዶክተር ኢሊባቡር አንድ አንድ የዪኒቨርሲቲ ሆስፒታሎች ላይ በድንገተኛ ክፍሎች የሚሞቱ ታካሚዎች ከ197 በመቶ በላይ የሚደርስበት ወቅት መኖሩን ያነሳሉ፡፡

የሞት ምጣኔው ከፍ የሚለው በቂ የህክምና ባለሙያ ባለመኖሩ፣በቂ የህክምና ክፍል ያለመኖሩ፣በቶሎ ሪፈር ለሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ሪፈር ያለማድረግ ተጠቃሽ ምክንያቶች መሆናቸውን ይናገራሉ፡፡

ስራ አስፈፃሚው በሀገሪቱ በተለያዩ ክልሎች የድንገተኛ ህክምና ውስጥ በርካታ ታካሚዎች ህይወታቸውን እያጡ መሆኑን ለጣብያችን አስረድተዋል፡፡

በዚህም ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር 37 ሚሊዮን ብር በጀት መድቦ ሆስፒታሎች ከሆስፒታል ጋር ጥምረት በመፍጠር ትልልቅ የሆኑ ሆስፒታሎች አነስተኛ ደረጃ ላይ ለሚገኙ ህክምና ተቋማት የሚረዱበት ሲስተም መፈጠሩ ተገልፃል፡፡

የድገተኛ ክፍል ሞትን ለመቀነስ፣ሰርጀሪ በአግባቡ እንዲሰራና ያለባቸውን የግብዓት እጥረት ለመቅረፍ የሚሰራ ሲስተም መሆኑም ተናግረዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ነሐሴ 23 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.