ከሰባት ዓመታት በኃላ ሳውዲ አረቢያ እና ኢራን አማባሳደሮቻቸውን ወደ ቦታቸው መልሰዋል፡፡

በቻይና አሻማጋይነት በመጋቢት ወር ላይ ያበቃው የሁለቱ ሀገራት ለሰባት ዓመታት ተቋርጦ የቆየው ግንኙነት ወደ ነበረበት ተመልሷል፡፡
በዚህም የሁለቱ ሀገራት አማባሳደሮች በትላንትናው ዕለት ወደ ሀገራቱ መግባታቸው የአርቲ ኒውስ ዘገባ ያሳያል፡፡

በሪያድ እና በቴህራን መካካል የነበረው ግንኙነት የተቋረጠው በፈረንጆቹ 2016 ዓ.ም የሪያድ መንግስት ሼህ ኒሚር አል ኒሚርን በስቅላት በመግደሉ የተነሳ በኢራን በተነሳ ተቃውሞ የሳውዲ ዲፕሎማቶች ላይ ጥቃት በመድረሱ ነበር፡፡

አማባሳደር አብዱላህ ወደ ቴህራን ከደረሱ በኃላ መግለጫ ያወጣው የሳውዲ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ግንኙነቱን ማጠናከር፣ግነኙነቱን አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

እንዲሁም ማክሰኞ ዕለት በሳውዲ አረቢያ የኢራን አምባሳደር የሆኑት አለሬዛ ኢናይቲ ሪያድ ሲገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሮች ባለስልጣናት እና የኢምባሲ ሰራተኞች አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲል የዜና ምንጩ ዘግቧል፡፡

ከመጋቢቱ የሁለቱ ሀገራት ስምምነት በኃላ ሳውዲ አረቢያ ከኢራን አጋር ከሆነቸው ሶሪያ የነበረውን ግንኙነት ወደነበረበት ለመመለስ እንዲሁም በየመን ሰላምን ለማምጣት እንደምትሰራ አስታውቃለች፡፡

በአቤል ደጀኔ
ጳጉሜ 02 ቀን 2015 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.