የፕሬዝዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር ለግብጽ የሚያደርገውን አመታዊ በጀት አጽድቋል፡፡
በዚህም ግብጽ 1.2 ቢሊዮን ዶላር ከአሜሪካ የምታገኝ ይሆናል፡፡
በዚህ አመት ግብጽ ከአሜሪካ ለወታደራዊ ድጋፍ የሚሆን 1.2ቢሊዮን ዶላር ድጋፍ ማግኝቷን ነው የተገለጸው፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ለግብጽ የሚደረገው ወታደራዊ ድጋፍ ማጽደቃቸውን የገለጸ ሲሆን፥ ካይሮ በአካባቢው ያላትን “ወሳኝ” ሚና አስምሮበታል።
ይህ ውሳኔ ግብጽ ለአሜሪካ የብሄራዊ ደህንነት የምታደረገውን ልዩ አስተዋጽ ያንጸባረቀ ነው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አንቶኒ ብሊንከን ተናግረዋል፡፡
ብሊንከን አክለው እንደተናገሩትም ግብጽ የአካባቢውን ሰላምና ደህንነት ለማስጠበቅ ወሳኝ መሆኗን በመግለጽ በተለይም በእስራኤል እና በፍልስጤም እንደዚሁም በሊቢያ እና በሱዳን እየተጫወተችው ያለው ሚና ቀላል የሚባል አይደለም ብለዋል፡፡
አሜሪካ በዓለም ዙሪያ ሰብአዊ መብቶች ለማስከበር ያላትን ቁርጠኝነት ለማረጋገጥ የምታደረገው ጥረት አጠናክራ ትቀጥላለች ሲሉ መደመጣቸውን አፍሪካን ኒውስ ዘግቧል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 04 ቀን 2016 ዓ/ም











