ጣሊያን በስደተኞች ተጨናንቃለች

በአንድ ቀን 7ሺህ ስደተኞች ጣሊያን መግባታቸው ተሰማ፡፡ይህንንም ተከትሎ የጣሊያኗ ጠቅላይ ሚኒስትር ጆርጂያ ሜሎኒ አስደንጋጭ ዜና ብለውታል፡፡ስደተኞቹ ወደ ጣሊያን የገቡት መነሻቸው ከቱኒዝያ አድርገው የላምፕዱሳ ደሴትን አቋርጠው እንደሆነ አፍሪካ ኒውስ አስነብቧል፡፡

ከስደተኞቹ መካከል አብዛኛዎቹ ከምስራቅ አፍሪካ ሃገራት ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ደግሞ የምዕራብ አፍሪካ ሀገራት ስደተኞች መሆናቸውን የጣሊያን የሃገር ወስጥ ሚንስትር ተናግረዋል፡፡

የጣሊያን የሃገር ውስጥ ሚንስትር አንድሪያ ኮስታ እንደተናገሩት በዚህ አመት ብቻ 120ሺህ ስደተኞች ወደ ጣሊያን መግባታቸው ገልጸው፣ ያሁኑ ክስተት ግን በታሪክ የመጀመርያው ነው ብለዋል፡፡

በአንድ ቀን ይሕንን ያህል ቁጥር ያለው ስደተኛ ሃገራቸው ገብቶ እንደማያዉቅ የተናገሩት ሚንስትሩ ነገሩ ከቁጥጥር በላይ እየሆነ መጥቷል ብለዋል፡፡የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሀገራት ስደተኞችን ወደ አውሮፓ እንዳይገቡ ስምምነት ቢያደርጉም ትብብር እያደረጉ አይደለም ብለዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

መስከረም 04 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.