በአማራ ክልል ዋግህምራና አካባቢዉ የመማር ማስተማር ሂደቱ ከተቋረጠ ከአራት ዓመት በላይ ሆኖታል ተባለ፡፡

ቀደም ሲል በኮሮና ቫይረስ ምክንያት፣ከዛም በሰሜኑ ጦርነት አማካኝነት ተቋርጦ የቆየዉ የመማር ማስተማር ሂደት፣ አሁንም መፍትሄ አለማግኘቱን ስብስብ ለሰብዓዊ መብቶች በኢትዮጵያ ዳይሬክተር ወይዘሮ መሠረት አሊ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

በአማራ ክልል በአሁኑ ሰዓት ያለው ግጭት ለሰብዓዊ መብት መከበር እና ሰብዓዊ እርዳታ ለማድረስ አስቸጋሪ መሆኑን ነገርዉናል።

በክልሉ ተባብሶ በቀጠለዉ ግጭት ምክንያት በአንድ አንድ አካባቢዎች ዋግህምራን ጨምሮ፣ ከአራት ዓመታት በላይ ትምህርት ተቋርጦ መቀጠሉ አሳሳቢ መሆኑን አንስተዋል።

አራት እና አምስት ዓመታትን ከትምህርት ገበታ መራቅ በትዉልዱ ላይ የሚያሳድረዉ ተፅዕኖ ከፍተኛ በመሆኑ መንግስት ትኩረት ሊያደርግበት ይገባል ብለዋል።

መንግስት በግጭት ዉስጥ ካሉ ታጣቂዎች ጋር ወደ ዉይይት በመምጣት በሰላማዊ መንገድ ችግሮችን እንዲፈታም ጥሪያቸዉን አቅርበዋል።

በአቤል ደጀኔ
መስከረም 07 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.