የሰዎችን ጤና ክፉኛ እየጎዳ ነው የተባለውና ለበርካታ አመታት የበረት አገልግሎት እየሰጠ የሚገኘው የሸጎሌ በረት ማእከል እንዲነሳ ተጠይቋል።

በረቱ ከቦታው እንዲነሳ የጠየቀው population health environment የተሰኘ በአካባቢ ጥበቃ ላይ የሚሰራ ድርጅት ነው።

ድርጅቱ በረቱ ለሚገኘበት ለጉለሌ ክፍለ ከተማ እና ለአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ደብዳቤ ማስገባቱንም ገልጿል።

ዜጎች ጤናማ እና ደህንነቱ በተጠበቀ አካባቢ የመኖር መብታቸው ሊጠበቅ እንደሚገባ ድርጅቱ አሳስቧል።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
መስከረም 21 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.