ካርቱም በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ፡፡

ሱዳን ካርቱም ውስጥ በሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ላይ በተፈጸመ የከባድ መሣሪያ ጥቃት ጉዳት መድረሱን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከኢምባሲዉ አረጋጧል፡፡

ይሁን እንጅ ጥቃቱ በሰዉ ላይ ምንም አይነት ጉዳት እንዳላደረሰ ከኤማባሲዉ ማረጋገጥ ችለናል፡፡

ዛሬ በተፈፀሙ ሁለት የአየር ጥቃቶች በኤምባሲዉ ቅጥር ግቢ የሚገኝ የዜጎች ማገገሚያና ማረፊያ ህንጻ መመታቱን ሰምተናል፡፡

በዚህም አንደኛዉ ሮኬት በህንፃዉ ላይ ጉዳት ሲያደርስ ሁለተኛዉ ደግሞ መሬት ላይ አርፏል ነዉ የተባለዉ፡፡

ከሁለት ሳምንት በፊት ተመሳሳይ የሚሳኤል ጥቃት በኤምባሲዉ ላይ ተፈፅሞ አንድ ሰዉ ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማድረሱንም ኤምባሲዉ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታዉቋል፡፡

በአባቱ መረቀ

መስከረም 22 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.