በኢትዮጵያ ውስጥ ከሚገኙ 14 መድሃኒት አምራች ኢንደስትሪዎች 6ቱ ምርታቸውን ወደ ውጭ ሃገራት መላክ ጀምረዋል ተባለ፡፡

ይህን የተናገሩት የኢትዮጵያ መድሃኒትና የህክምና መገልገያዎች አምራች ኢንደስትሪዎች ዘርፍ ማህበር ፕሬዘዳንት ዶ/ር ዳንኤል ዋቅቶሌ ናቸው።

በአሁኑ ወቅት ያለውን የመድሃኒት አቅርቦት እና ፍላጎትን ለማመጣጠን የተለያዩ ስራዎች በመሰራት ላይ እንደሚገኝ የተናገሩት ሃላፊው፣ ከእዚያም አልፎ ኢትዮጵያን የአፍሪካ መድሃኒት አቅርቦት ማዕከል ለማድረግ መታቀዱንም ገልፀዋል።

ከእዚህ በተጨማሪም ከውጪ ለሚገቡ የመድሃኒት ምርቶች ፈተና የሆነውን የውጪ ምንዛሪ እጥረትን ጨምሮ፣ ሌሎች የዘርፉ ችግሮችን ለመፍታት የጤና ሚኒስቴር ከሚመለከታቸው አጋር አካላት ጋር በቅርበት እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በቀጣዮቹ ጊዜያት 60 ከመቶ የሚሆነውን የመውሃኒት ምርት በኢትዮጵያ ለመሸፈን መታቀዱም ተነግሯል።

20ኛ ዓመታዊ ጉባኤውን ያደረገው ኢትዮጵያ መድሃኒትና የህክምና መገልገያዎች አምራች ኢንደስትሪዎች ዘርፍ ማህበር ይፋ ባደረገው መረጃ፣ በአሁኑ ወቅት መገኛቸውን በኢትዮጵያ ካደረጉ 14 መድሃኒት አምራቾች ውስጥ 6ቱ ወደ ተለያዩ ሀገራት ምርቶቻቸውን መላክ እንደጀመሩ አስታውቋል።

በረድኤት ገበየሁ

ጥቅምት 05 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.