በከተማዋ ያለው የውሃ ችግር ከእውነታው በእጅጉ ተጋኖ እየተነገረ ነው ሲል የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን ወቀሰ፡፡

ባለስልጣኑ ችግር መኖሩን አምኖ ግን ተጋኖ እየተነገረ ነው ብሏል፡፡

ከሰሞኑ የመጠጥ ውሃ ከ15 እና ከ20 ቀን በላይ በሰፈራችን ይጠፋል፤ ከፍተኛ ችግር ውስጥ ነን ሲሉ፣ በመዲናችን የሚገኙ ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

በተለይም በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ሳሪስ አቦ አከባቢ፤ቦሌ ቡልቡላና፤ በአራዳ ክፍለ ከተማ የተወሰኑ ሰፈሮች የውሃ ችግር አለባቸው ተብሎ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ቅሬታ ከቀረበባቸው ቦታዎች ተጠቃሾች ናቸው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም ከዚሁ ጋር በተያያዘ የአዲስ አበባ ውሃ እና ፍሳሽ ባለስልጣን መስሪያ ቤትትን ያነጋገረ ሲሆን ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ ይህን ያህል የተጋነነ የውሃ ችግር በከተማዋ የለም ሲል ምላሽ ሰጥቷል፡፡

ከሰሞኑ ግን በቦሌ ቡልቡላ አንድ የውሃ ጉድጋድ በመቃጠሉ፣ በሰፈሩ የፈረቃ መዛባት መከሰቱን፣ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰርካለም ጌታቸው ገልጸዋል፡፡

ከዛ ውጭ በከተማው ባሉ በሁሉም ቦታዎች በተለመደው የፈረቃ ሂደት ለነዋሪው የንጹህ መጠጥ ውሃ እየቀረበ ነው ብለዋል፡፡

ውሃ በመስመር በማይደርስባቸው ቦታዎች ደግሞ በቦቴ መኪና እናደርሳለን ያሉት ዳይሬክተሯ፣ ማህበረሰቡ በሳምንት ከአንድ እስከ ሶስት ጊዜ ውሃ ያገኛሉ ብለዋል፡፡

በመሳይ ገ/መድህን
ጥቅምት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.