ኢትዮጵያ ዉስጣዊ አንድቷን ባጣችበት ወቅት የተነጠቀችዉን ወደብ ተመሳሳይ ችግር ዉስጥ ሆና ጥያቄዉን ማንሳቷ ተገቢ እንደማይሆን ምሁራን ተናገሩ፡፡

አሁን እንደ ሀገር ትኩረት ሊሰጠዉ የሚገበዉ ነገር የሰላሙ ጉዳይ መሆኑንም ምሁራኑ አስረድተዋል።

በባህር ዳር ዩንቨርሲቲ የፖለቲካል ሳይንስና የአለም አቀፍ ግንኙነት መምህር አቶ አበበ ይርጋ ከጣቢያችን ጋር ባደረጉት ቆይታ፤ በርግጥ ኢትዮጵያ የባህር ባር እንደሚያስፈልጋት ግልፅ ቢሆንም ነገር ግን ከወደቡም ከምንም በላይ ዉስጣዊ ሰላምን ማስፈን ይቀድማል ብለዋለ።

በጂግጂጋ ዩንቨርሲቲ የህግና ፖለቲካ ሳይንስ መምህሩ አቶ ሰለሞን ጓዴ በበኩላቸው ፤ ሀገራዊ አንድነቱ ሲረጋገጥ ያኔ ኢትጵያ ያጣቻቸዉን ብሄራዊ ጥቅሞች በዲፕሎማሲም ሆነ በሃይል አማራጭ መጠየቅ ይቻላል ነው ያሉት።

አቶ ሰለሞን ኢትዮጵያ ከዚህ ቀደም የነበሯትን ወደቦች ያጣችው ውስጣዊ አንድነቷ በተዳከመበት ጊዜ እንደሆነ አስታውሰው በተመሳሳይ ወቅላይ ሆና አሁን ላይ መጠየቅ መሞከር ዘላቂ መፍትሔ አያመጣም ነው ያሉት ።

በመሆኑም የውስጥ ችግሮችን በመፍታት ሀገራዊ አንድነቱን ማፅናት ይቀድማል ብለዋል።

ሁለት ነገሮች ላይ ትኩረት ማድረግ የግድ ይላል የሚሉት ምሁራኑ ፣ እነሱም የሀገር ዉስጥ ሰላምና ዲፕሎማሲ ናቸው ብለዋል።

በቀይ ባህር ክልል ወሰነ-ሰፊ ይዞታ የነበራት ኢትዮጵያ፣ በየዘመናቱ ህዝቦቿ በከፈሉት መሪር መስዋዕትነት ነፃነቷንና ክብሯን ጠብቃ የኖረች ሀገር ነች።

አዶሊስ፣ ዘይላ እና ምፅዋን የመሳሰሉ ወደቦች በኢትዮጵያ ግዛት ሥር እንደነበሩ በርካታ የታሪክ ሰነዶች ያረጋግጣሉ።

ይሁን እንጂ በሀገር ወስጥ የፖለቲካ ድክመትና የዉጭ ሃይሎች በተለያየ ወቅት የሰሜኑን የሀገሪቱን ግዛት በመቆጣጠር ኢትዮጵያን ከቀይ ባህር ክልል በማራቅ የበይ ተመልካች እንድትሆን አድረገዋታል፡፡

ለዚህ ደግሞ የኢትዮ ኤርትራ ጦርነት ትልቅ አስተዋጽኦ እንዳደረገ ይነገራል፡፡

ታዲያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ ከሰሞኑ በሰጡት ማብራሪያ ኢትዮጵያ ከቀይ ባህር ተጠቃሚ ልትሆን ይገባል ማለታቸዉ የሚታወስ ነዉ፡፡

በአባቱ መረቀ

ጥቅምት 06 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.