በአነስተኛ የቅጣት እርከን ላይ ያሉ የትራፊክ ህጎች ሊሻሻሉ ነው።

የቅጣት እርከናቸው ከ100 ብር የሚጀምሩ የትራፊክ ህጎች ሊሻሻሉ መሆኑም ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል።

ህጎቹ የሚሻሻሉት አሽከርካሪዎች ተገቢው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ነው ተብሏል።

ህጎቹን የሚያሻሽለው ደግሞ የኢትዮጵያ የመንገድ ደህንነት እና መድን ፈንድ አገልግሎት ነው።

የአገልግሎቱ የኮሚኒኬሽን ባለሙያ አቶ በለጠ አሰፋ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት፣ አንዳንድ የትራፊክ ህጎች እና የቅጣት ደረጃቸው እየተሻሻለ ይገኛል ብለዋል።

አሽከርካሪዎች በሚያጠፉት ጥፋት ልክ የትራፊክ ቅጣቱ እንደሚሻሻል የተናገሩት አቶ በለጠ፣ አላማው አሽከርካሪዎች ጥንቁቅ እንዲሆኑ ማስቻል መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

በአነስተኛ የቅጣት እርከን ለይ ያሉት የትራፊክ ህጎች አሽከርካሪዎችን በሚፈለገው ልክ እያስተማራቸው ባለመሆኑ፣ ህጎቹን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ መገኘቱን ተናግረዋል፡፡

ባለሙያው ማሻሻያው የቅጣት መጠኑን በምን ያል መጠን ሊጨምር እንደሚችል ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.