በፍልስጤም የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከ4 ሺህ በላይ መድረሱ ተገለጸ፡፡

በእስራኤል -ፍልስጤም ግጭት ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች 4ሺህ 6መቶ 51 መድረሱን የፍልስጤም ጤና ሚኒስቴር አስታውቋል።

ከሟቾቹ መካከል 1ሺህ 8መቶ 73ቱ ህፃናት እና 1ሺህ 23ቱ ደግሞ ሴቶች መሆናቸው ነው የተገለጸው።

በጦርነቱ ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ14ሺህ መብለጡንም ጨምሮ ገልጿል።

በእስራኤል -ፍልስጤም ግጭት ህይወታቸው ያለፉ እስራኤላውያን ቁጥር ደግሞ 1ሺህ 4መቶ መድረሱም ተገልጿል።

ጦርነቱ ተባብሶ የቀጠለባት ጋዛ በከፍተኛ የሰብዓዊ ቀውስ ውስጥ ናት የተባለ ሲሆን ውሃ ፣ መብራት ፣ ምግብ እና የመድኃኒት አቅርቦት መጠን እያለቀ መምጣቱ ተገልጿል።

በእስከዳር ግርማ

ጥቅምት 12 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.