ሀገር አድን ዉይይት እንዲካሄድ ብጠይቅም ከመንግስት አዎንታዊ ምላሽ አላገኘሁም ሲል እናት ፓርቲ ገለጸ።

ሀገር አድን ዉይይት ለማድረግ ለመንግስት ጥሪ ካቀረቡት አምስት ፖርቲዎች ዉስጥ አንዱ የሆነዉ የእናት ፖርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዳዊት ብርሃኑ እንዳሉት፣ጥሪው በመንግሥት ተቀባይነት በማጣቱ ዉይይቱ መካሄድ እንዳልቻለ ተናግረዋል።

የሀገራችንን የፖለቲካ ሁኔታ ቀድመን ተረድተን ነበር የሚሉት አቶ ዳዊት፣ የሀገራችን ችግር በሰላማዊ ዉይይት እንጂ በነፍጥ የሚፈታ እንዳልሆነ በመረዳት ተደጋጋሚ ጥሪዎችን ቢያደርጉም በመንግስት በኩል ተቀባይነት ማጣቱን አስረድተዋል።

ሀገራዊ የሰላም ዉይይቱ ሁሉም በሀገሪቷ ዉስጥ የሚንቀሳቀሱ አካላት ነፃ በሆነ መንገድ ጥያቄያቸዉን ወደ ጠረጴዛ በማምጣት ሰላማዊ ዉይይት ለማካሄድ የታሰበ ነበር ብለዋል ሃላፊዉ።

ጥሪያችንን አሁንም ቀጥለናል ያሉት ሃላፊው፣በተለይም በአዲስ አበባ መቀመጫቸዉን ካደረጉ የዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጋር በመሆን ግፊታቸዉን እንደሚቀጥሉ የተናግረዋል፡፡

ሐምሌ 6 2015 በተሰጠዉ መግለጫ ጥምረት የፈጠሩት አምስት ፖርቲዎች ማለትም ኢህአፓ፣መኢአድ፣እናት ፓርቲ፣የአማራ ግዮናዊ ንቅናቄ እና አንድ ኢትዮጵያ ዲሞክራሲ ፓርቲ፣ በኦሮሚያ ክልል ታጥቀዉ ከሚንቀሳቀሰውና በሽብርተኝነት ከተፈረጀው ሸኔ እና በአማራ ክልል ከመንግስት ጋር ጦርነት ዉስጥ የገቡት መንግስት ኢ-መደበኛ ብሎ ከጠራቸዉ አካላት ጋር፣ እንዲሁም በመላዉ ኢትዮጵያ ከሚንቀሳቀሱ ድርጅቶች ጋር ሀገር አድን ወይይት በአንድ ወር ዉስጥ እንዲካሄድ ጠይቀዉ እንደነበር የሚታወስ ነዉ።

በአቤል ደጀኔ

ጥቅምት 19 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.