የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እያዘጋጀ ያለዉ የመገበያያ ፕላትፎርም በቀጣዮቹ 3 ወራት ዉስጥ እንደሚጠናቀቅ ገለጸ፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮ ቴሌኮም ጋር በመተባበር እያዘጋጀ ያለዉ የመገበያያ ፕላትፎርም በ2 ወይም 3 ወራት ጊዜ ዉስጥ ተጠናቆ ወደ ስራ እንደሚገባ ኢትዮ ኤፍ ኤም ሰምቷል፡፡

መገበያያዉ ኢንዱስትሪዎችን ከኢንዱስትሪዎች ጋር፣ ከግብዓት አቅራቢዎች እና ከተጠቃሚዎች ጋር የሚያገናኝ እንደሆነ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ተናግረዋል፡፡

በመካከል ላይ ያሉ ደላላዎችን በማስወጣት ቀጥታ አቅራቢ እና አምራች እንዲሁም አምራች እና ተጠቃሚ የሚገናኙበት መሆኑንም አክለዋል፡፡

ክፍያዉም ቀጥታ ይሆናል ያሉት ሚኒስትሩ፣ እያንዳንዱ ተጠቃሚ የኢንዱስትሪ ምርቶችን በቀጥታ የሚያገኝበት የመገበያያ ፕላትፎርም መሆኑን ነው የገለጹት፡፡

ዝግጅቱ በዚህ ሁለት እና ሶስት ወራት ጊዜ ዉስጥ ተጠናቆ ወደ ስራ እንደሚገባም ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በከፍተኛ ደረጃ አሁን ላይ በትኩረት እየሰራባቸዉ ከሚገኙ ሁለት ጉዳዮች መካከል በአገሪቱ የሚገኙ ኢንዱስትሪዎች ላይ ቆጠራ ማካሄድ እና ይህንን የመገበያያ ፕላትፎርም ወደ ስራ ማስገባት መሆኑንም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ጥቅምት 22 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.