ሳምሰንግ በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች ወደ ኢትዮጵያ ለመምጣት መዘጋጀቱን አስታውቋል።

በአለማችን በኤሌክትሮኒክስ ገበያው ታዋቂ የሆነው”Samsung electronics “በ2024 ወደ ኢትዮጵያ በአዳዲስ ቴክኖሎጂዎች እንደሚመጣ ገልጿል።

በብዛት በስልክ እና በተያያዥ ምርቶች የሚታወቀው “samsung” አሁን ደግሞ በአዲስ የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ መምጣቱን አስታውቋል።

ድርጅቱ በንግድ ስም መጠሪያው በሆነው”samsung” የመኖሪያ ቤትን ጨምሮ የስራ ቦታን የአየር ሆኔታ መቆጣጠር የሚችል ማሽን ማምረት መጀመሩን ነው የገለፀው።

ባለንበት ሆነን በእጅ ስልኮቻችን መቆጣጠር የምንችለው የአየርን ሙቀትም ሆነ ቅዝቃዜን መቆጣጠሪያ ማሽኑ ላለንበት ቦታ የተረጋጋ እና ሰለማዊ ከባቢን ይፈጥርልናል ተብሏል።

ከአየር ግፊት እና ከሚረብሽ ድምፅ ነፃ ነው የተባለለት ይህ ማሽን እስከ 15 ሜትር ርቀት በመሄድ ለአከባቢው ተፈላጊውን አየር
እንደሚሰጥ ተቋሙ አስታውቋል።

በተለይ ይህ የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂ በዋናነት የጤና ተቋማትን ጨምሮ ለግል እና ለመንግስት ተቋማት በልዩነት መቅረቡ ተገልጿል።

በተጨማሪም ከዋስትና ጋር ያሉ የልብስ ማጠቢያ ፣ዘመኑን የዋጁ አዳዲስ የስልክ ምርቶች ፣ፍሪጅ፣ለህንፃዎች የሚሆኑ ሊፍቶች እና የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ቴክኖሎጂዎችን ከፈረንጆቹ 2024 ጀምሮ ለሃገራችን ገበያ እንደሚያቀርብ “samsung” ገልጿል።

በመሳይ ገ/መድህን

ጥቅምት 28 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.