ኬንያውያን 100 ሚሊዮን ችግኞችን ለመትከል የዛፍ ተከላ በዓል ሊጀምሩ ነው፡፡

የኬንያ መንግስት በ10 አመታት ውስጥ 15 ቢሊየን ችግኞችን የመትከል እቅድ አካል የሆነው እና ኬንያውያን 100 ሚሊዮን ዛፎችን መትከል የሚችሉበት ልዩ የበዓል ቀን ሊጀመር መሆኑ ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የኬንያ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር በዓሉ የመከበሩ ምክንያት እያንዳንዱ ኬንያዊ የእንቅስቃሴው ባለቤት እንዲሆን ታስቦ ነዉ ብሏል፡፡

እያንዳንዱ ኬንያዊ ቢያንስ ሁለት ችግኞችን እንዲተክል ለማድረግ እየተሰራ ነዉ የተባለ ሲሆን ፣ ይህም የታሰበዉን የ100 ሚሊየን ችግን ተከላ አላማ ለማሳካት ያስችላል ተብሏል፡፡

ይህ ጅምር የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል የታሰበ ስለመሆኑም ነዉ የተገለጸዉ፡፡

የአገሪቱ መንግሥት ወደ 150 ሚሊዮን የሚጠጉ ችግኞችን በሕዝብ ማቆያ ጣቢያዎች እያቀረበ ሲሆን፤ችግኞቹን በተለያዩ ማዕከላት አማካኝነት በተመረጡ የህዝብ ቦታዎች እንዲተክሉም በነፃ እየተሰጠ ይገኛል።

የችግኝ ተከላዉ እንቅስቃሴ በኢንተርኔት ክትትል የሚደረግበት ሲሆን ይህም ግለሰቦች እና ድርጅቶች የተተከሉትን የእጽዋት ዝርያዎች፣ ቁጥር እና ቀን ጨምሮ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ እንዲመዘግቡ በማድረግ ነው።

‹‹ጃዛ ሚቲ››የተሰኘ የሞባይል መተግበሪያን በመጠቀም እንዲተክሉ እየተደረገ ሲሆን፤ መተግበሪያዉ ቦታውን ከተገቢው ዝርያ ጋር በማዛመድ ተገቢውን ችግኝ እንዲተክሉ የሚያግዝ መሆኑንም የአገሪቱ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በእስከዳር ግርማ

ህዳር 03 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *