እስራኤል በጋዛ እያካሄደችው ባለው ጦርነት በቀን 260 ሚሊዮን ዶላር ታወጣለች ተባለ።

ይህ መጪ የእስራኤልን ኢኮኖሚ ክፍኛ አየጎዳው በመሆኑ ተጨማሪ 75 በመቶ ብደር ልትበር እንደምትችል ተነግሯል።

እስራኤል በጋዛ ሰርጥ ላይ እየወሰደች ባለው ጥቃት ጦርነቱ በቅድሚያ ከተገመተው ከፍተኛ በላይ ውጪ እያስወጣት መሆኑን ብሉምበርግ አስነብቧል።

ጦርነቱ ወደ 8 ቢሊዮን ዶላር የሚጠጋ ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ያደረሰ በመሆኑ በዚህኛው ህዳር ወር 75 ከመቶ ከተበደረችው የበለጠ በቀጣይ ለመበደር ማቀዷን የእስራኤል የፋይናንስ ሚኒስቴር አስታውቋል።

እስካሁን እስራኤል በጋዛ ላይ በወሰደችው ጥቃት 488 ቢሊየን ዶላር ኢኮኖሚዋ ጉዳት
ያስከተለ ሲሆን በተለያዩ የከተማ ግዛቶች በሺዎች የሚቆጠሩ የንግድ ሥራዎች ተቋርጠዋል።

እስራኤል ይህ ጦርነት ለሚያመጣው ማንኛውንም ኢኮኖሚያዊ ጉዳት ዋጋ ትከፍላለች ሲሉ ኔታንያሁ ተናግረዋል።

የውል ሰው ገዝሙ
ህዳር 04 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.