ኩባንያዉ በኢትዮጵያ በጀመረዉ የቴሌኮም አግልግሎት በአጭር ጊዜ ዉስጥ የደንበኞቹን ቁጥር ከ4 ሚሊዮን በላይ ማድረሱን አስታወቋል፡፡
አዲሱ የኩባንያዉ ስራ አስፈፃሚ አስፈጻሚ ዊም ቫንሄልፑተን በሰጡት መግለጫ በቴሌኮምና በፋይናንስ ዘርፍ ትኩረት ሰጥተን እየሰራን ነዉ ብለዋል፡፡
ዋና ሰራ አስፈፃሚዉ ከቴሌኮም በተጨማሪም በፋይናስ ዘርፉ 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ደንቦች እንዳሉ ተናግረዋል፡፡
አሁን ላይ 35 በመቶ ለሚሆነዉ የኢትዮጵያ ህዝብ ተደራሽ የሚሆን የቴኬኮም መሰረተ ልማት መዘርጋቱንም አንስተዋል፡፡
በአሁን ጊዜ ኩባንያዉ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል 2 ሺህ የቴሌኮም ማማ መሰረተ ልማቶች እንዳሉት ተገልጧል፡፡
በቀጣይ ሁለት አመታትም ቁጥሩን ወደ 7 ሺህ ከፍ እንደሚያደርግም ዋና ስራ አስፈጻሚዉ አስታዉቀዋል፡፡
ለዚህም እስከ ሁለት ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ገንዘብ እንደተመደበ በመግለጫቸዉ አንስተዋል፡፡
ኩባንያዉ ሀገር ዉስጥ ያለዉ የፖለቲካ አለመረጋጋት ስራዉን በተገቢዉ መንገድ እንዳይሰራ እንዳደረገዉም ተነስቷል፡፡
በአባቱ መረቀ
ሕዳር 06 ቀን 2016 ዓ.ም











