ይህን ሪፖርት ይፋ ያደረገው የአለም ባንክ ነው።
የአለም ባንክ የትምህርት ጥራትን፣ትምህርት የሚያቋርጡ ተማሪዎችን እንዲሁም የትምህርት ቤት የተማሪዎች ምገባን በተመለከተ ከፌደራል እና ከክልል የትምህርት ቢሮ ሃላፊዎች ጋር ምክክር አድርጓል።
የአለም ባንክ የኢትዮጵያ ትምህርትን በተመለከተ ባደረገዉ ጥናት 90 በመቶ የሚሆኑት የአስር አመት ልጆች በአግባቡ ማንበብ የማይችሉ ናቸው ብሏል።
ከአራተኛና አምስተኛ ክፍል ተማሪዎች መካከል በትክክል ማንበብ የሚችሉት 1 በመቶ ብቻ መሆናቸዉንም ጥናቱ አመልክቷል።
ድርጅቱ ለዚህ በምክንያትነት ካነሳቸው ነጥቦች መካከል ልጆች በቶሎ ትምህርት ቤት አለመግባታቸው ዋነኛ ምክንያት ነው ብሏል።
በተጨማሪም በከተማ እና በገጠሪቱ የሃገሪቱ አካባቢዎች ለትምህርት ያለው አመለካከት ዝቅተኛ መሆንም በምክንያትነት ተጠቅሷል፡፡
ሃገሪቱ በትምህርት ዙሪያ ከተደራሽነት ባሻገር ጥራት ላይ ከፍተኛ ትኩረት ሰጥታ መስራት እንደሚጠበቅባትም ዓለም ባንክ ጥናት አመላክቷል፡፡
በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ሕዳር 07 ቀን 2016 ዓ.ም











