ባለሥልጣናት ስለባህር በር የሚሰጡት መግለጫ የተጠናና በጥንቃቄ መሆን እንዳለበት ምሁራን አሳሰቡ፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባዘጋጀው የጥናት መድረክ ላይ፣ ጥናት ያቀረቡና ውይይት ያደረጉ ምሁራን፣ መንግሥት ስለባህር በር የሚሰጣቸው መረጃዎች የጎረቤት አገሮችን የማያሠጉና ጥንቃቄ የተሞላባቸው እንዲሆኑ አሳስበዋል፡፡

‹‹ፍትሐዊ የወደብ አጠቃቀም ለአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ ሰላምና ልማት›› በሚል ርዕስ በተስተናገደው በዚህ ዓውደ ጥናት ላይ፣ ኢትዮጵያ በሰላማዊ መንገድ የባህር በር ባለቤት መሆን ስለምትችልባቸው አማራጮች ሰፊ ምሁራዊ ውይይት መካሄዱን የሪፖርተር ዘገባ ያመለክታል፡፡

በጥናት መድረኩ ላይ ለኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄን በማስመለስ ታሪካዊ ድል ያስመዘገቡ ያለፈው ትውልድ ምርጥ ተሞክሮ ታሪካዊ ድል እንደነበር በጉልህ ተነስቷል፡፡

በሰላማዊ መንገድ ኤርትራን በፌዴሬሽን ከኢትዮጵያ ጋር በማስተሳሰር የባህር በር ጥያቄን የመለሰ ትውልድ ያፈራችው ኢትዮጵያ፣ ይህን ታሪካዊ ስኬት ማስቀጠል የሚችል ተተኪ ትውልድ ማፍራት ባለመቻሏ የባህር በር አልባ ሀገር ሆና እንደቀረች ጎልቶ ተነስቷል፡፡

ከዚህ ጎን ለጎን አሁን ላይ የባህር በርና ወደብን በተመለከተ ግብታዊ አስተያየቶች ሲሰጡ እንደሚሰማ ያነሱ አንዳንድ ተወያዮች፣ ይህ ያልተጠናና ጥንቃቄ የጎደለው አካሄድ ሰላም የናፈቃትን ኢትዮጵያ ከጎረቤቶቿ ጋር ወደባሰ ችግር ውስጥ እንዳይካተት አስጠንቅቀዋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን

ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.