የግብር የስነ-ምግባርና መሰረታዊ የታክስ ህግ ትምህርት በከፍተኛ የትምርት ተቋማት ሊሰጥ ነዉ ተባለ::

የገቢዎች ሚኒስቴር የግብር ተገዢነት የስነምግባር ችግርን ለመቅረፍ እንዲያስችል መሰረታዊ የታክስ ህግ በከፍተኛ የትምርት ተቋማት የትምርት ስርዓት ውስጥ እንዲካተት እየሰራ እንደሚገኝ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታወቋል፡፡

ሚኒስተሩ ለዩንቨርስቲዎች የማሰልጠኛ ማኗል እያዘጋጀ እንደሚገኝ በገቢዎች ሚኒስተር የታክስ ጉዳዮች ትምህርት ዳይርክቶሬት ዳይሬክተር አቶ በፍርዱ መሰረት ተናግረዋል፡፡

የሰው ልጅ ህግን እንዲያከብር መማር ነው ያለበት የሚሉት ዳይሬክተሩ መሰረታዊ የታክስ ህጉ ከ1ኛ ክፍል እስከ 12ተኛ ባለው የትምህርት ስርዓት ውስጥ ተካቶ ይገኛል ብለዋል፡፡

ይህም ስርዓት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ደረጃ መካተት እንደሚገባው ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው የመንግሰት ቢሮዎች ጋር ባደረገው ውይይት መተማመን ላይ እንደደረሰ ገልጸለዋ፡፡

ስለሆነም የገቢዎች ሚኒስተር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የማሰልጠኛ ማኗል እያዘገጀ እንደሚገኝ አቶ በፍርዱ መሰረት ተናግረዋል፡፡

በተጨማሪም ለግብር ከፋዮች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ የገለጹት፤ዳይሬክተሩ አምናና ዘንድሮ በተሰጠ ስልጠና ከ5 ሺህ 5 መቶ በላይ ግብር ከፋዮችን ማስመረቅ ተችሏል ብለዋል፡፡

የስነ ምግባር ችግር ባለባቸዉ የግብር ሰብሳቢ አካላት ላይ እርምጃ እያተወሰደ እንደሚገኝ አነስተዋል፡፡

ነገር ግን በስነምግባር ጉዳይ እርመጃ የተወሰደባቸውን የግብር ሰብሳቢ ባለሞያዎችን ኩጥር ከመናገር ተቆጥበዋል፡፡

በመሳይ ገ/መድሕን

ህዳር 10 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *