ኢትዮጵያን ጨምሮ የብሪክስ አባል ሀገራት መሪዎች በጋዛ  ጉዳይ ሊመክሩ  ነዉ

በኢራን ጥያቄ አቅራቢነት መሰረት ደቡብ አፍሪካ በምታዘጋጀዉ በዚህ  ጉባኤ ላይ  የብሪስ አባል ሀገራት መሪዎች እንደሚመክሩ  ታዉቋል፡፡

ዉይይቱ  በቨርቿዋል እንደሚደረግና  የሩሲያዉ ፕሬዝዳንት  ቭላድሚር ፑቲን  እንደሚሳተፉም  የአርቲ ኒዉስ  ዘገባ  ያሳያል፡፡

በቅርቡ በደቡብ አፍሪካዉ የብሪስ ጉባኤ ላይ   በአዲስ አባልነት   ጎራዉን የተቀላቀሉት ሳዉድ አረቢያ፤ አርጀንቲና፤ ግብጽ ኢትዮጵያ  ፤ኢራንና  የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች እንደሚሳተፉ   ፕረስ ቴሌቪዥን ዘግቧል፡፡

ኢራን ሁሉም የአለም ሀገራት  ከእስራኤል ጋር ያላቸዉን ማንኛዉንም አይነት ግንኑነት  እንዲያቋርጡም  ጠይቃለች

እስራኤል በጋዛ እያደረሰች ያለችዉን ጥቃት ለማስቆም ሁነኛዉ መፍትሄ  ሀገራት ከእስራኤል ጋር ያላቸዉን የንግድ የዲፕሎማሲና የፖለቲካ  ግንኙነት ማቆም ብቻ ነዉ ሲሉ  የኢራኑ ፕሬዝዳንት ኢብራሁም ራይሲ  ተናግረዋል፡፡

ፕሬዝዳንት  ራይሲ   ለ50 ሀገራት መሪዎች   ደብዳቤ መላካቸዉንም  አስታዉቀዋል፡፡

አባቱ መረቀ
ህዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.