የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ /አህአፓ/ እና የእናት ፓርቲ ከሽግግር ፍትህ በፊት የሽግግር መንግስት እንዲቀድም ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የሁለቱ ፓርቲ አመራሮችም የሽግግር ፍትህ ያለ ሽግግር መንግስት መሳካት እንደማይችል ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡
የኢህአፓው ተቀዳሚ ምክትል ሊቀመንበር የሆኑት መጋቢ ብሉይ አብርሃም በኢትዮጵያ ውስጥ በገለልተኝነት ሊዳኝ የሚችል ተቋም የለም ያሉ ብለዋል።
የፍትህ ተቋሞቻችንም ነፃና ገለልተኛነታቸው የሚያጠያይቅ በመሆኑ የሽግግር መንግስት ለፍትህ መረጋገጥ ይረዳል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ከባድ ወንጀል የፈፀሙ አካላት ተጠያቂ ካልሆኑና ስልጣን የሚያሰጣቸው ከሆነ የሽግግር ፍትህ ማረጋጥ አይቻለም ብለዋል፡፡
የእናት ፓርቲው ህዝብ ግንኙት ሀላፊ አቶ ዳዊት ብርሃኑ በበኩላቸው በሀገሪቱ አሁን ባለው ውጥንቅጥ እና ችግር አንፃር ከሽግግር ፍትህ ቀድሞ የሽግግር መንግስት እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል፡፡
የሽግግር መንግስት ባልተቋቋመበት ሁኔታ የሽግግር ፍትህን ማረጋገጥ አይቻልም ያሉ ሲሆን ገዢው ፓርቲ እየመራው ባለው ሁኔታ ትክክለኛ የሽግግር ፍትህ መፍትሄ ይሆናል ብለው እንደማያምኑ ለጣብያችን ተናግረዋል፡፡
አቤል ደጀኔ
ህዳር 11 ቀን 2016 ዓ.ም











