ደቡብ አፍሪካ ከእስራኤል ጋር የነበራትን ዲፕሎማሲያው ግኑኝነት አቋረጠች፡፡

ደቡብ አፍሪካ የእስራኤል ኤምባሲ እንዲዘጋ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷ እንዲቋረጥ ወሰነች፡፡

የደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት በፕሪቶሪያ የሚገኘው የእስራኤል ኤምባሲ እንዲዘጋ እና ከእስራኤል ጋር ያለ ሁሉም ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት እንዲቋረጥ ወሰነ።

በእስራኤል ላይ ከፍተኛ ተቃውሞ ስታሰማ የነበረችው የደቡብ አፍሪካ ምክር ቤት ይህንን ውሳኔ ያሳለፈው ማክሰኞ ዕለት ባካሄደው ስብሰባ ነው።

በዚህም መሠረት የአገሪቱ ምክር ቤት አባላት በደቡብ አፍሪካ የሚገኘውን የእስራኤል ኤምባሲ ለመዝጋት እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ለማቋረጥ ድምጽ ሰጥቷል።

የፓርላማውን አብላጫ ወንበር የያዘው ገዢው አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ ፓርቲ እስራኤል በጋዛ የምታደርገውን ወታደራዊ ዘመቻ አጥብቆ ሲተች ቆይቷል።

አገሪቱ ከትናንት በስቲያ ሰኞ ዓለም አቀፉ የወንጀል ፍርድ ቤት በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤኒያሚን ኔታኒያሁ ላይ የእስር ትዕዛዝ እንዲያወጣም ጠይቃ ነበር።

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

ህዳር 12 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.