በሰሜናዊ የጋዛ ሰርጥ አሁን ላይ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት 3 ሆስፒታሎች ብቻ ናቸው ሲል የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታዉቋል፡፡

እነዚህ ሆስፒታሎች ወደ 9መቶ ሺህ ለሚጠጉ ሰዎች አገልግሎት እየሰጡ ይገኛልም ነዉ ያለዉ ሚኒስቴሩ፡፡

የጋዛ ጤና ጥበቃ ሚኒስቴር “መድሃኒቶች እና የህክምና ቁሳቁሶች ለጋዛ በከፍተኛ መጠን ሊቀርቡ ይገባል” ብሏል፡፡

የአራት ቀናት የተኩስ አቁም እረፍት እና የሰብዓዊ ድጋፍ ቢኖርም በሰሜናዊው የጋዛ ሰርጥ አሁን ላይ አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙት 3 ሶስት ሆስፒታሎች ብቻ ናቸዉ ተብሏል፡፡

ለጋዛ ሰርጥ የደረሰው የህክምና እርዳታ እና የነዳጅ መጠንም በቂ አይደለም ነዉ የተባለዉ፡፡

በተለይም በሰሜናዊ የጋዛ ክፍል ያሉ ሆስፒታሎች ካሉበት አስከፊ ሁኔታ አንጻር በጣም ውስን እና በቂ አይደሉም ሲሉ የሆስፒታሉ ዋና ዳይሬክተር ለአናዶሉ ተናግረዋል።

አክለውም መድሃኒቶች እና የህክምና መገልገያዎች በጋዛ ውስጥ ካለው አስከፊ የጤና ሁኔታ አንጻር በብዛት ሊቀርቡ ይገባል ብለዋል ።

በጋዛ የሚገኘው የመንግስት የሚዲያ ቢሮ እንዳለው 26 ሆስፒታሎች እና 55 ጤና ጣቢያዎች ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል። የእስራኤል ጦር 55 አምቡላንሶች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ሌሎች በደርዘን የሚቆጠሩ ደግሞ በነዳጅ እጥረት ምክንያት ከአገልግሎት ውጪ ሆነዋል ብሏል።

በኳታር አሸማጋይነት ለአራት ቀናት የሚቆይ የሰብአዊ ድጋፍ ማድረጊያ እረፍት ዓርብ የተፈጸመ ሲሆን፤ ይህም እስራኤል በጋዛ ላይ የምታደርሰዉን ጥቃት ለጊዜው ለማስቆም እና ለተከበበው የጋዛ ሰርጥ ተጨማሪ ዕርዳታን ለማድረስ ነበር፡፡

በእስራኤል እና ሃማስ በአራት ቀናት የተኩስ አቁም ስምምነት የመጀመሪያዎቹ ሁለት ቀናት ውስጥ በተደረጉ ሁለት የእስረኞች ልዉዉጥ፤ 41 እስራኤላውያን እና የውጭ ዜጎችን ለ78 ፍልስጤማውያን ቅያሪ መደረጉን አናዶሉ ዘግቧል፡፡

በእስከዳር ግርማ

ህዳር 17 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.