ያለ አግባብ ምርት ሲያከማቹ የተገኙ  ነጋዴዎች ላይ  እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ አስታወቀ

በመዲናዋ ያለአግንብ ምርት ሲያከማቹ የተገኙ  ላይ  እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ሰውነት አየለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል።

ቢሮው  የምርት  እጥረት ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚሰራ የተገለጸ ሲሆን ሆን ብለው ምርትን ያለአግባብ በማከማቸውት በአቋራጭ ለመክበር የሚደረግ  የነጋዴዎች የንግድ እንቅስቃሴ  ከመዓከል ጀምሮ እስከ ወረዳ በቢሮው  በኩል ምርቶች ይከማቻሉ ተብልው በሚታሰቡ መጋዘኖች ላይ ድንገተኛ ፍተሻ እንደሚደረግ ተናግረዋል።

በቢሮ ምርትን ያለአግባብ ሲያከማቹ የተገኙ ነጋዴዎች ላይ ከፅሁፍ ማስጠንቀቂያ፣ እስከ ማሸግ እና   ምርቶቹን ለህብረተሰቡ እንዲከፋፈሉ የተደተገበት ሆኔታ መኖሩን ገልጸው   ህብረተሰቡ የምርት ክምችት የሚያከናውኑ ግለሰቦችን ሲመለከቱ ጥቆማዎችን እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

በእሌኒ ግዛቸው
ህዳር 21 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.