“የኔ” የተሰኘ ሳይንሳዊ ክህሎት ማጎልበቻ ድረገፅ ይፋ ተደርጓል፡፡

በብሬክስሩ ትሬዲንግ ይፋ የተደረገው ይህ ድረገጽ፣ኬንያ ከሚገኘው የንዛ እና ከደቡብ አፍሪካ ስታንዳርድ ባንክ ጋር በመተባበር የተመሰረተ መሆኑ ታውቋል፡፡

ድረገጹ ሰዎች ያላቸውን ክህሎት ሳይንሳዊ በሆነ መልኩ በሚያገኙት ስልጠና ራሳቸውን እንዲያውቁና ባላቸው ውስጣዊ ፍላጎትና ክህሎት ላይ ተመስርተው የወደፊት ህይወታቸውን ቀደምው ማስተካከል እንዲችሉ ትልቅ እገዛ የሚያደርግ መሆኑ ተመላክቷል፡፡

የብሬክስሩ ትሬዲንግ የቦርድ ስብሳቢ ነፃነት ዘነበ እንደተናገሩት፣በኢትዮጵያ በትምህርቱ ዘርፍ ካሉት ችግሮች መካከል ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ገብተው ለመሰልጠን በውስጣቸው ካለ አቅም፣ፍላጎትና ችሎታ ይልቅ የስራ እድል እንዳለው የሚታሰበውን የትምህርት ዘርፍ መርጦ መቀላቀል አንዱ ነው፤ይህ ደግሞ በህይወታችን ማበርከት የሚገባንን ትልቅ ስራ እንዳንሰራ ያደርገናል ብለዋል፡፡

የዚህ ድረ-ገጽ አንዱ አላማም ቀድሞ ግንዛቤውን በመፍጠር ይህን ችግር መቀነስ መሆኑን አንስተዋል፡፡በተጨማሪም በተለያዩ ኩባንያዎች ተቀጥረው የሚሰሩ ሰራተኞች ያሉባቸውን ክፍተቶች በመለየት ስራቸውን እየሰሩ ክህሎቱን እንዲያዳብሩና ስራቸው ላይ ብሎም በህይወታቸው ላይ አዎንታዊ ለውጥ እንዲያመጡ ያስችላቸዋል ነው ያሉት፡፡

ድረገጹ በየትምህርት አይነቱ ከያዛቸው ስልጠናዎች በተጨማሪ ከ4 ሺህ በላይ የክህሎት ስልጠናዎችን በተጨማሪነት በነፃ በበይነ መረብ የሚያቀርብ ስለመሆኑም ይፋ በተደረገበት ወቅት ተነስቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮጵያዊያን
ህዳር 24 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.