በአሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ነዋሪዎች በጸጥታ ችግር ምክንያት የደረሱ ሰብሎችን መሰብሰብ ባለመቻላቸዉ ሰብሎቹ እየተበላሹ መሆናቸዉን ተናገሩ፡፡

ግድያ ፤እገታ፣ መፈናቀልና ድህነት አሁንም ችግር ሆነዉ በቀጠሉባት ደራ ወራዳ፣ ሰብሎች ባለመሰብሰባቸዉ የከፋ ችግር እያንዣበባት መሆኑን ነዋሪዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም ቅሬታቸዉን አሰምተዋል፡፡

ከጣቢያችን ጋር ቆይታ ያደረጉ የወረዳዋ ነዋሪዎች ወቅቱ የደረሱ ሰብሎች የሚሰበሰቡበት ቢሆንም እራሱን የኦሮሞ ነጻ አዉጪ ብሎ በሚጠራዉ ሃይል ምክንያት ሰብሎቹን መሰብሰብ እንዳልቻሉ አስረድተዋል፡፡
ነዋሪዎቹ አሁን ላይ የደረሱ ሰብሎች እየተበላሹ መሆናቸዉንም ተናግረዋል፡፡

ከአዲስ አበባ ከተማ 220 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘዉ ደራ ወረዳ በሽብር ቡድኑ ምክንያት ለከፍተኛ ችግር እንደተዳረረገች ነዋሪዎች ይነገራሉ፡፡

ወረዳዋን ከአማራ ክልል መርሃቤቴ ወረዳ ጋር ያገናኝ የነበረዉ አማራጭ መነገድም በአማራ ክልል ባለዉ የጸጥታ ችግር ምክንያት መንገዱ መዘጋቱን ሰምተናል፡፡

እናም የወረዳዋ ነዋሪዎች ለከፍተጫ የኢኮኖሚ ችግር እንደተጋለጡ ጠቅሰዉ ፤የሰብሎች አለመሰበስብ ደግሞ ችግሩን ያባብሰዋል ብለዋል፡፡

ከሰብል አለመሰብሰቡ በተጨማሪ ንፁሃን ዜጎች ለሞት፤ ለእገታና ለመፈናቀል መዳረጋቸዉን የሚናገሩት ነዋሪዎቹ፤ የሚመለከተዉ አካል በአስቸኳ፤ ይድረስልን ሲሉ ተማጽነዋል፡፡

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የምትገኘዉ ደራ ወረዳ በጤፍ ምርት የምትታወቅ እንደሆነ ሰምተናል፡፡

በአባቱ መረቀ
ህዳር 25 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.