የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር በክልሉ የተከሰተው ርሃብ እያስከተለው ያለውን አደጋ ለመከላከል በክልሉ የአስቸኳይ አደጋ ጊዜ አዋጅ ማወጁን አስታውቋል።

የጊዜያዊ አስተዳደሩ ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ፣ በክልሉ በአምስት ዞኖች፣ በ32 ወረዳዎችና በ196 ቀበሌዎች ድርቅና የሰብዓዊ ዕርዳታ እጦት የፈጠሩት ከፍተኛ ርሃብ በስፋት ማጋጠሙን ገልጸዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ፣ በክልሉ የተከሰተውን ድርቅና ርሃብ ለመከላከል ክልል ዓቀፍ እንቅስቃሴ ለማድረግ የሚያግዝ ውይይት ከተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች ተወካዮች ጋር ውይይት ማድረጋቸውን ተናግረዋል።

ረድዔት ድርጅቶች በክልሉ በድርቅና ርሃብ ለተጎዱ ወገኖች 20 በመቶ ብቻ የሰብዓዊ ድጋፍ እንደጀመሩ ተነግሯል።

ድርቁ ባስከተለው ርሃብ የሚሞቱ ሰዎችን ቁጥር ለመቀነስ፣ በአገር ውስጥ እና በውጭ የሚገኙ ወገኖች የሚያደርጉትን ደጋፍ የሚያስተባብር ኮሜቴ በቅርቡ ይቋቋማል ነው የተባለው፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የኢትዮያዊያን

ህዳር 27 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.