ከኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ ተፈናቅለው ደብረ ብርሃን ከተማ የሚገኙ ዜጎች ለከፍተኛ ችግር መዳረጋቸውን ተናገሩ፡፡

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን ዱግዳ ወረዳ ወዮ ገብርኤል ቀበሌ ይኖሩ እንነበሩ የሚገልፁት ዜጎቹ የታጠቁ ሃይሎች የሚያደርሱትን ግድያ እገታና ዝርፊያ በመሸሽ ሀብት ንብረታቸዉን በተለይም የደረሱ ሰብሎችን ጭምር ሳይሰበስቡ ህይዎታቸዉን ለማትረፍ ወደ ደብረ ብርሃን መሄዳቸዉን ለኢትዮ ኤፍ ኤም ተናግረዋል፡፡

እነዚህ ተፈናቃይ ዜጎች ቤታቸውና አዝመራቸዉ እንደተቃጠለባቸዉም ይናገራሉ፡፡

አብዛኞቹ በአካባቢዉ ተወልደዉ አድገዉና ንብረት አፍርተዉ ይኖሩ እንደነበር የሚገልፁት እነዚህ ዜጎች፤ አካባቢዉ ሞቃታማ በመሆኑ የደብረ ብርሃንን ቅዝቃዜ በተለይም ልጆቻቸዉ መቋቋም ባለመቻላቸዉ ለስቃይና ለህመም እንደተዳረጉም ነግረዉናል፡፡

መጠለያና አልባሳት ማጣታቸዉ ደግሞ ሁኔታዉን የከፋ አድርጎብናል ነዉ ያሉት፡፡

ከመሰከረም ወር ማብቂያ ጀምሮ ወደ ደብረ ብርሃን መግበታቸዉን የሚናገሩት ተፈናቃዮቹ የመግብ፤ የመጠለያና የአልባሳት ድጋፍ እንዲደረግላቸዉ ለሚመለከታዉ አካል ብናሳዉቅም እስካሁን ምላሽ አላገኘንም በመሆኑም የሚመለከተዉ አካል ቢደርስልን ሲሉም ተማጽነዋል፡፡

እኛም ለመሆኑ ተፈናቃቹን ወደ ጊዚያዊ መጠለያ በማስገባት ድጋፍ እንዲረግላቸዉ ምን እየተሰራ ነዉ ስንል የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደርን ጠይቀናል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የስነ ህዝብ አማካሪና የጊዚያዊ መጠለያዎች አስተባባሪ አቶ አንተነህ ገብረ እግዚያብሄር ተፈናቃዮችን በመመዝገብ ወደ ጊዚያዊ መጠለያ ካምፖች ዉስጥ ለማስገበት ከሚመለከለተዉ አካላት ጋር ዉይይት እየደረገ ነዉ ተብሏል፡፡

ከምስራቅ ሸዋ ተፈናቅለዉ ወደ ደብረ ብርሃን ከተማ የገቡት 5 መቶ አባወራዎች መሆናቸዉን የነገሩን አቶ አንተነህ ይህም ተጨማሪ ቀዉስ የሚፈጥር ነዉ ብለዋል፡፡

አሁን ላይ ከእነዚህ ተፈናቃይ በተጨማሪ በደብረ ብርሃን ሶስት መጠለያ ካምፖች ዉስጥ ከ29 ሺህ በላይ ዜጎች የሰዉ እጅ በመጠባበቅ ላይ ናቸዉ በተለይም የምግብ አቅርቦት በመደበኛነት አለመኖር ደግሞ ዋነኛዉ ችግር ነዉ ተብሏል፡፡

በአባቱ መረቀ

ታህሳስ 02 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.