ከ100 በላይ አምራች ኢንተርፕራይዞች የሚሳተፉበት ኤግዚብሽን እና ባዛር በአዲስ አበባ ከተማ ተከፈተ፡፡

ኢትዮጵያም ታምርት ፤እኛም እንሸምት” በሚል መሪ ቃል ኤግዚብሽን እና በዛሩ “የኛ ምርት” የሚል ስያሜ ተሰጥቶት ከዛሬ ጀምሮ እስከ እሁድ ይካሄዳል ተብሏል፡፡

በኤግዚቢሽን እና ባዛሩ የጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፤የፕላስቲክ፤የቆዳና የቆዳ ውጤቶች ፤አግሮ ፕሮሰሲንግ አምሮቾች፤የኩሚካል ውጤት አምራቾች፤የማእድን እና ጌጣ ጌጥ ውጤት አምራቾች፤የእንጨት እና ብረታ ብረት ውጤት አምራቾች እንደሚሳተፉበት ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም ከ50 ሺህ በላይ ገዢ እና ጎብዢዎች ይጠበቃሉ ብሏል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን በሃገራዊ የምርት ቅቡልነት፤በአምራች ኢትርፕራይዞች ኢኮኖሚያዊ ሚናና በፋይናንስ አቅርቦት ዙሪያ ያተኮሩ ወይይቶች እንደሚደረጉ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት አስታወቋል፡፡

ከዚህ ባለፈ የኢትዮጵያ ኢንተርፕራይዝ ልማት የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪው አሁን ያለውን 6.9 በመቶ የኢኮኖሚ ድርሻን በቀጣይ አመታት ወደ 17.2 ለማሳደግ እየሰራ መሆኑን አስታውቋል፡፡

አሁን ያለውን 50 በመቶ አማካይ አምራች ኢንዱስትሪዎች የማምረት አቅማቸውን ወደ 85 በመቶ ለማሳደግ እየሰራ እንዳሚገኝ የኢንተርፕራይዝ ልማቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አለባቸው ንጉሰ ተናግረዋል፡፡
የኢንዱስትሪው ዘርፍ አሁን ከደረሰበት 405 .6 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ግኝት፤ወደ 9 ቢሊዮን ዶላር ለማሳደግ ተቋሙ እየሰራ እንደሚገኝ አስታውቀዋል፡፡

በመሳይ ገብረ መድህን

ታህሳስ 03 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *