በኢትዮጵያ የሲቪከ ማህበረሰቡን እንቅስቃሴ ለመገደብ የሚደረግ የሀሰት ውንጅላ እንደሚያሳስባቸው በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አዎር ተናገሩ፡፡

በኢትዮጵያ የሲቪክ ማህበረሰቡን እንቅስቃሴ ለመገደብ የሀሰተኛ ውንጀላ ጥቅም ላይ ይውላል፤ ይህም ምህዳሩ እንዲጠብ አድርጎታል ብለዋል አምባሳደር ስቴፈን አዎር ፡፡

አምባሳደሩ ይህንን ያሉት ባለፈው እሁድ መብቶችና ዲሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) 75ኛ የሰብዓዊ መብቶች ቀንን ባከበረበት ወቅት ነው፡፡

ስለ ኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ስንነጋገር ስለ ሰብዓዊ መብቶች መከበር ቅድሚያ ሰጥተን ማሰብ አለብን ያሉት አምባሳደሩ፣ ኢትዮጵያ እንድትበለፅግም ሆነ ደህንነቱ የተጠበቀ የስራ ከባቢ ለመፍጠር፣ ሰብዓዊ መብቶች መከበራቸው መረጋገጥ አለበት ብለዋል፡፡

ሰብዓዊ መብቶች መከበር እንዲሁም ለእኩልነትና ለፍትህ መታገል ጠንካራ ዲሞክራሲያዊት ኢትዮጵያን ለመገንባት ጠቃሚ መሆኑ እሙን ነው ሲሉ አምባሳደሩ ተናግረዋል፡፡

አምባሳደሩ በኢትዮጵያ የሲቪክ ምህዳሩ መጥበብና በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች፣ሚዲያዎችና የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ ሁሉም ባለድርሻ አካላት ላይ የሚጣሉ እገዳዎች ያሳስቡናል ብለዋል፡፡

የሰብዓዊ መብቶች አለመከበር የሀገሪቱን ሲሞክራሲያዊ መሠረት በቀጥታ ይጎዳዋል ያሉ ሲሆን ለዚህም ጀርመን ሰብዓዊ መብት ድርጅቶች መደገፍ ወሳኝ ነው ብላ ታምናለች በማለት ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያሉ የሰብዓዊ መብቶች መከበር ላይ የሚሰሩ ተቋማትን ጀርመን በተለያዩ መንገዶች ላይ ትደግፈዋለች ብለዋል፡፡

በአቤል ደጀኔ

ታህሳስ 04 ቀን 2016 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.